AMN- ግንቦት 12/2018 ዓ.ም
በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን ፔጅ አዲስ አበባ ገብቷል።
ዲላን ፔጅ በቲክቶክ ብቻ ከ19 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ አዲስ አበባ መግባቱን አስመልክቶ ባስተላለፈዉ መልእክት በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችዉ ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ ብሏል።

ግርማ ሞገስ ያለው መልክዓ ምድር፣ በርካታ የታሪክ እና የሃይማኖት እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ መሆኗን ተናግሯል፡፡
ተፅዕኖ ፈጣሪዉ ዲላን ፔጅ ለተከታዮቹ፤ “ከምነግራችሁ ይልቅ ባሳያችሁ ይሻላል” በማለት ቀጠሮ ይዟል።
ኢትዮጵያ በርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ያሏት ሀገር መሆኗን እንደሰማ ጠቅሶ፣ ከእነሱ ጋርም ልዩ ጊዜ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።

የዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የስበት ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባም ዲላን ፔጅን እንኳን ደህና መጣህ ብላ ተቀብላዋለች፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ