AMN- ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
ከ2 ዓመት በፊት 10 በመቶ ድርሻውን ለገበያ ያቀረበው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ባለፉት ጊዜያት የአክሲዮን ሽያጭ ሲያካሂድ እና የአክሲዮኖችን መረጃ ሲያጣራ መቆየቱን ገልጿል።
ድርጅቱ ለገበያ ያቀረበውን የ10 በመቶ ድርሻ ከ47 ሺህ በላይ ሰዎች የገዙ ሲሆን፣ 45 ሺህ የሚሆኑት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሰፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
እነዚህ ማረጋገጫ ያገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ባለ አክሲዮኖች አክሲዮናቸውን በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በኩል መሸጥ፣ መለወጥ እና ማስተላለፍ እንደሚችሉም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።
አክሲዮኑን ከገዙት ደንበኞች መካከል 96 በመቶዎቹ ማረጋገጫ ሲያገኙ፣ የተቀሩት ደግሞ ብሄራዊ መታወቂያን ባለማያያዝ እና ኢትዮጵያዊ ባለመሆናቸው ማረጋገጫ ሳያገኙ መቅረታቸውም ተነግሯል።

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ ለገበያ ያቀረበው የ10 በመቶ ድርሻ የተፈቀደው ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሲሆን፣ በቀጣይ ግን ለውጭ ዜጎች ሊያቀርብ እንደሚችልም ተናግረዋል።
ድርጅቱ ለገበያ ካቀረበው ድርሻ ውስጥ 10.7 ሚሊየን ድርሻ ሲሸጥ 10.1 ሚሊየኑ መረጋገጫ አግኝቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሸጠው ድርሻ 3.2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡም ተነግሯል።
በአሰግድ ኪዳነማሪያም