በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሃገሪቱን የሚመራ መንግሥት ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

You are currently viewing በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሃገሪቱን የሚመራ መንግሥት ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

የተሰጣቸውን ዲሞክራሲያዊ መብት በመጠቀም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚወክላቸውን መንግሥት ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ኤ ኤም ኤን ፕላስ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት፥ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሃገሪቱን የሚመራ መንግሥት ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሰጣቸው መብት በመጠቀም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እቅዳቸውንና ማኒፌስቷቸውን በተለያዩ ቋንቋዎች ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናገሩት ነዋሪዎቹ ይህም የሚበጃቸዉን ፓርቲ ለመምረጥ እድል እንደፈጠረላቸዉ ጠቁመዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች በአደባባዮች ጭምር የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸው የዲሞክራሲ ምህዳር እየሰፋ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚሸጋገርበትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚያንጸባርቅ መሣሪያ በመሆኑ፥ የምርጫ ካርድ ያወጣ ማንኛውም መራጭ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚወክለውን መንግሥት መምረጥ እንዳለበትም አሳስበዋል።

በደረጀ በየነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review