AMN— ሰኔ 2/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ጉዞ ወደፊት ነው። ጠላት የፈለገውን ያህል ቢያቅድ ከጉዟችን እንደማያስቆመን ወልድያ ምስክር ናት ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በታሪካዊቷ፣ በየጁዎች ሥልጣኔ መገኛ በሆነችው ወልድያ ከተማ በመገኘት፣ አመራርና ሕዝብ በአንድነት ተግቶ ያሳካቸውን የልማት ፕሮጀክቶች መርቀናል ብለዋል።

ወልድያ የልማት፣ የፅናትና የድል አምባ ናት! ከተማዋን የማዘመን፣ የኮሪደር ልማትን የማስፋፋት፣ የሕዝብና የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍትን የመገንባት እንዲሁም የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላትን እውን የማድረግ ሥራዎቻችን ወደፊት የመገስገሳችን ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።

መንገዳችን መደመር፣ ግባችን ደግሞ ብልጽግና ነው! ትግላችን መንገዳቸውን ክፍፍል፣ ግባቸውን ድህነት ካደረጉ ቆሞ-ቀሮች ጋር በመሆኑ የኢትዮጵያን ልዕልና ሳናረጋግጥ አንቆምም፤ ሺህ ጠላት ቢሰበሰብ የኢትዮጵያን ጉዞ ለአፍታም አያስቆመውም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡