ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ አስጀመሩ

AMN-ሰኔ 8/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የዚህን ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠን፣ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጭው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራዎን ያኑሩ! ሲሉም በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review