AMN-ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በምድብ ዘጠኝ የምትገኘው ፈረንሳይ ኢራቅን 3ለ0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች።
በመጥፎ የአየር ፀባይ ምክንያት 2 ሰዓት በተገፋው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።
የሪያል ማድሪዱ አጥቂ በዓለም ዋንጫው 16 ግቦች ላይ በመድረስ ከሚረስላቭ ክሎሰ ጋር 2ኛው የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል። የ27 ዓመቱ አጥቂ 18 ግቦች ባሉት ሊዮኔል ሜሲ ብቻ ይበለጣል።
ቀሪውን የፈረንሳይ ግብ የፓሪሰን ዠርማው የፊት መስመር ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ማስቆጠር ችሏል።

በመጀመሪያ ጨዋታዋ ሴኔጋልን 3ለ1 ያሸነፈችው ፈረንሳይ የጥሎ ማለፍ ዙሩን ተቀላቅላለች። በምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋ ኖርዌይን የምትገጥም ይሆናል።
ሁለተኛ የዓለም ዋንጫዋን እየተሳተፈች የምትገኘው ኢራቅ በቀጣይ ከሴኔጋል ጋር ትጫወታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ