AMN-ሰኔ 16/2018 ዓ.ም

ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ኧርሊንግ ሃላንድ እያሳዩት ባለው ብቃት ብዙዎች ጠየቁ ክሪስቲያኖ ሮናልዶስ? ብለው።
ፖርቹጋል ከዲ.ሪ ኮንጎ ጋር በደካማ ብቃት 1ለ1 ስትለያይ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለቡድኑ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ይበዛል የሚሉ ድምፆች በስፋት ተናፈሱ።

ሮናልዶ 23 ዓመት በሞላው የፕሮፌሽናል እግርኳስ ሕይወቱ ለበርካታ ተጠራጣሪዎቹ ምላሽ ሰጥቷል። በዚህም የዓለም ዋንጫ ይህን ማድረግ ጀምሯል።

ፖርቹጋል ኡዝቤኪስታንን እየገጠመች በምትገኝበት ጨዋታ 3ለ0 እየመራች የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
ከሦስቱ ግቦች ሁለቱ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሆነው ተመዝግበዋል። ይህም በስድስት የዓለም ዋንጫዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች አድርጎታል።

በአጠቃላይ በዓለም ዋንጫ ውድድር ያስቆጠራቸው 10 ግቦች ዘጠኝ ግብ ያለው ዩዞቢዮን በልጦ የሀገሩ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን አስችሎታል።
ከኡዝቤኪስታን ጋር እየተደረገ ባለው ጨዋታ ኑኖ ሜንዴዝ ሌላኛውን ግብ ለፖርቹጋል አስገኝቷል።
በሸዋንግዛው ግርማ