AMN- ሰኔ 30/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ ዐሻራ እና የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “የፓርላማ ቆይታችንን ተከትሎ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነናል፤ በዚህ የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት ተስፋን መትከላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የሕግ አውጪው አካል እና አስፈጻሚው አካል በሀገራዊ የልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስትራቴጂ ላይ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የአፈር መሸርሸርን ለማስቆም እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመላ ሀገሪቱ እየተተገበረ ይገኛል፡፡
መርሃ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመላው ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በያዝነው የችግኝ ተከላ ወቅት ብቻ 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡
በትዝታ መንግስቱ