AMN- ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 502.27 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የበጀት ረቂቅ አጸደቀ፡፡
ከበጀቱ 359.3 ቢሊየን ብር ለካፒታል ወጪ የተመደበ ሲሆን ፣ 142.97 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ የተመደበ ነው፡፡

ከበጀት ድልድሉ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው የካፒታል በጀት 71.5 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን ፣ 25.27 በመቶው ለመደበኛ ወጪ የተመደበ ነው፡፡ 16 ቢሊየን ብር ደግሞ ለመጠባበቂያ በጀት ተይዟል፡፡
በጀቱ የከተማዋን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ ሲሆን ፣ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከፍተኛ ድርሻ የያዘው የካፒታል በጀቱ ለስራ እድል ፈጠራ፤ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት፤ ለመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የትራስንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻልና አጠቃላይ የከተማዋን ልማትና እድገት ይበልጥ ለማዘመን የተመደበ መሆኑ ተመላቷል፡፡
ታደሠ ሽፈራው