በጀቱ የከተማዋን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም

በከተማችን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የከተማ አስተዳደራችን የ2019 በጀት 502. 27 ቢሊዮን ብር አድርገን አፅድቀናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የበጀቱ 71 .53 % በዋናነት ለድህነት ቅነሳ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለእድገት ተኮር ዘርፎች ( ለካፒታል ወጪ ) የሚውል ይሆናል ብለዋል።

ለአስተዳደራዊ ወጪ ብር 142.97 ቢሊዮን (25.27%) መመደቡን ጠቅሰዋል፡፡

ለመጠባበቂያ ወጪ ብር 16.00 ቢሊዮን (3.18%) ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የ2019 በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ152.26 ቢሊዮን ብር (43.5%) እድገት እንዳለው ነው በመልዕክታቸው ያሰፈሩት።

በጀቱ የከተማዋን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ ሲሆን ፣ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚውል ይሆናል ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review