የከተማዋ ስኬቶች የኢትዮጵያን የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል

You are currently viewing የከተማዋ ስኬቶች የኢትዮጵያን የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል

AMN- ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የኢትዮጵያን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው በጎ ልምዱን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም የእመርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ያለፉት 5 ዓመታት እመርታዎች ” የኢትዮጵያ ማንሰራራት ” የሚል ስነድ ቀርቦ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ፤ ከተሞች ሸማቾች እንጂ አምራች አይደሉም የሚለውን አመለካከት መቀየሩን አዲስ አበባ ከተማ ማሳያ ናት ብለዋል፡፡

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንዳስጠበቁ ሁሉ የእኛ ትውልድም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች አከናውኗልም ነው ያሉት፡፡

በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንደገለጹት፤ የጳጉሜን ቀናት የቀደሙ ስኬቶችን በማስታወስ ለቀጣይ ስራዎች ይበልጥ ስኬታማ ለመሆን ዝግጅት የሚደረግበት ነው፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review