የዳግማዊ ሚኒሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከ500 በላይ የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ

You are currently viewing የዳግማዊ ሚኒሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከ500 በላይ የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ

AMN- መስከረም 09/2019 ዓ.ም

ዳግማዊ ሚኒሊክ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአንስቴዢያ፣ በነርሲንግ፣ በኢመርጀንሲ ክሊኒካል ነርሲንግ፣ በሜዲካል ላብራቶሪ፣ እንዲሁም በሚድዋይፍሪ እና በሌሎች የጤና ዘርፎች በ14 የቅድመ ምረቃ እና በ3 የድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 556 የጤና ባለሙያዎች አስመረቀ።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አለሙ ዳንኤል፣ ኮሌጁ ለ60ኛ ጊዜ የጤና ባለሙያዎችን እያስመረቀ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም በቅድመ ምረቃ 334 ሴቶች እና 141 ወንዶች፣ እንዲሁም በድሕረ ምረቃ 42 ሴቶች እና 39 ወንድ ተማሪዎች መመረቃቸውን ገልጸዋል።

በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ፤ ከተማ መስተዳድሩ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ከተማ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አያይዘውም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ በጤናው ዘርፍ የሚታዩትን ክፍተቶች ለመድፈን ተመራቂዎች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በበሃይሉ አያሌው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review