በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN- መስከረም 11/2019 ዓ.ም

‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ ዘጠኝ ዙር በረራ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 34 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

‎ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ103 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review