የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ አባላት ከመደበኛ ስራዎቻቸው በተጨማሪ ከማህበረሰቡ እና ከመደበኛ ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀልን ሊከላከሉ ይገባል

You are currently viewing የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ አባላት ከመደበኛ ስራዎቻቸው በተጨማሪ ከማህበረሰቡ እና ከመደበኛ ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀልን ሊከላከሉ ይገባል

AMN- ኅዳር 2/2019 ዓ.ም

አይነት እና ቅርጻቸውን እየለዋወጡ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት ትልቅ ሚና እንዳላቸው የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው ለግል እና ለመንግስት የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት በፀጥታና በወንጀል መከላከል ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፤ አይነት እና ቅርጻቸውን እየለዋወጡ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲ አባላት ሚናቸው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚደረገው ቅድመ የወንጀል መከላከል ስራም በከተማዋ የሚፈጸም ወንጀል እንዲቀንስ ማድረጉን በመግለጽ ተፈጽሞ ሲገኝም እርምጃ ለመውሰድ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ብለዋል።

የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ አባላት ከመደበኛ ስራዎቻቸው በተጨማሪ በሥራ አካባቢያቸው ላይ ከማህበረሰቡ እና ከመደበኛ ፀጥታ አካላት ጋር ወንጀልን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ባለው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሁም የገጽታ ግንባታ ላይ የግል እና የመንግስት የቅጥር ጥበቃ አባላት ድርሻቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review