የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ፣ በሰላም፣ በደስታና በልዩ ድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ፣ በሰላም፣ በደስታና በልዩ ድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- መስከረም 23/2019 ዓ.ም

ኢሬቻ የምስጋና፣ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ሕያው መገለጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትሰስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከባህላዊ እሴቱ ባሻገር፣ የተለያዩ ሕዝቦች በፍቅርና በወንድማማችነት የሚገናኙበት፣ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቻችን የሚጎሉበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።

የኢሬቻን እሴቶች በተግባር በመግለጽ፣ አቅሞቻችንን አስተባብረንና አንድነታችንን አጽንተን፣ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ለሀገራዊ መግባባትና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በጋራ እንትጋ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዓሉ በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ሁሉ፣ በተለይም እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በፍቅር ያስተናገዳችሁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን፣ አባገዳዎችን፣ ሃደ ሲንቄዎችን፣ ፎሌዎችን፣ የጸጥታ አካላትንና አመራሮቻችን፣ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ! ብለዋል፡፡

ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት! ኢሬቻ ለሰላምና ለአንድነት!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review