ታላቁ ሩጫ በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ በትኩረት ይሠራል – አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

You are currently viewing ታላቁ ሩጫ በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ በትኩረት ይሠራል – አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

AMN – ኅዳር 13/2019 ዓ.ም

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ በትኩረት እንደሚሠራ የውድድሩ መሥራች አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ገለጹ።

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ “ሩጫዬ ቀለሜ” በሚል መሪ ሐሳብ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ ከ61 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በታደሙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

10 ኪሎ ሜትር በሸፈነው ውድድር በወንዶች ይስማው ድሉ፣ ታከለ ሞሴ እና ሮባ መርጋ፤ እንዲሁም በሴቶች የኔዋ ንብረት፣ አልማዝ ዮሐንስ እና ዓለምነሽ ጥላዬ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

በዘንድሮው ውድድር ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ሦስት ሺህ ተማሪዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አትሌት ኃይሌ፣ መርሐ ግብሩ ከአበበ ቢቂላ አንስቶ የቀጠለውን የኢትዮጵያን የረጅም ርቀት ሩጫ የድል ጉዞ ለማስቀጠልና ተተኪዎችን ለማፍራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

የዘንድሮው ውድድር ኢትዮጵያ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማዘጋጀት እንደምትችል በተግባር ያሳየ መሆኑን ጠቁመው፤ ለውድድሩ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለባለድርሻ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review