በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አዲስ የተሾሙት ኃላፊ የስራ ርክክብ አደረጉ

AMN መስከረም 25 ቀን /2019 ዓ.ም

አዲስ የተሾሙት የቢሮ ኃላፊ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አቶ ጥላሁን ከበደ ከቀድሞው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ኃላፊነቱን የተረከቡ ሲሆን በሁለቱ ኃላፊዎች መካከል የሥራና የሰነድ ርክክብ ተካሂዷል።

የቀድሞው ቢሮ ኃላፊ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በተቋሙ በነበራቸው የሥራ ቆይታ የነበረውን መልካም የሥራ ጊዜ እና ስራዎች ለማሳከት የነበረውን የጋራ ጥረት በማንሳት፣ ለአዲሱ ቢሮ ኃላፊ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቢሮ የቀድሞው ኃላፊ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ላለፉት ጊዜያት በተቋሙ የተከናወኑ ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸሞች ፣ የተጀመሩ ስራዎችን እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን የሚያሳይ የሥራ ርክክብ ሰነድ ለአዲሱ ቢሮ ኃላፊ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ለአቶ ጥላሁን ከበደ አስረክበዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አቶ ጥላሁን ከበደ የተጣለባቸውን አደራና ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ ለመወጣትና የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና የተቋሙን አገልግሎት ይበልጥ በመስራት የከተማዋን ነዋሪ የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በቢሮው የቀድሞ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፍ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ የቢሮውን ተግባራት እና የታቀዱና የተጀመሩ ስራዎችን እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለአዲሱ አመራር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ለአቶ ጥላሁን ከበደ ማቅረባቸዉን ቢሮዉ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review