በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

AMN – ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ እና በምስራቅ ጎጃም ዞን በተለያዩ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ከማለዳው ጀምሮ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ በደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ከሚሴና ሌሎችም ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሰልፈኞቹ የሰራዊቱን ህዝባዊነትና ጀግንነት እንዲሁም የሀገር መከታ መሆኑን የሚያሳዩ መፈክሮች፤ የሀገር ብሄራዊ ጥቅምና በተለይም የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄን የሚያንጸባርቁ መልእክቶችን እያስተጋቡ ይገኛሉ፡፡

በሰልፉ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review