ለሰላም እጅ ስጡ – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

You are currently viewing ለሰላም እጅ ስጡ – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

AMN – ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም

የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሰላም እጅ ስጡ ፣ ፖለቲካ እና ስልጣንን ከፈለጋችሁ ተደራጁና በሰላማዊ መንገድ ተወዳደሩ ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ሲከበር ባደረጉት ንግግር ፣ መከላከያ ሠራዊት ሰባት የጽምዶ ቡድኖችን ፣ የትብብር ሀይሎችን ፣ ሶስት የጀርባ የውጭ ሀይሎችን አሸንፏል የቀጠናው አሰማማኝ ኃይልም ሆኗል ብለዋል፡፡

በመከላከያ ሰራዊት መቃብር ላይ የምትመሰርቱት ሽግግር መንግስት የለም ፣ ለሰላም እጅ ስጡ ፣ ፖለቲካ እና ስልጣንን ከፈለጋችሁ ተደራጁና በሰላማዊ መንገድ ተወዳደሩ ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ በአቋራጭ መንገድ ከባንዳ ጋር ሆናችሁ ስልጣንን ከጫካ ለማግኘት መሞከር ከንቱ ምኞት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review