ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚን አነጋገሩ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚን አነጋገሩ

AMN – ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ ስራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ በውይይታችንም መንግሥት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማስቀጠልና ለማፋጠን እየሠራቸው ያሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸውልኛል ብለዋል።

ሁዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ፣ በተለይም በአይሲቲ መሠረተ ልማትና በግንኙነት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞም ከሁዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ በደህንነትና በአካባቢያዊ እሴት ፈጠራ መርሆዎች ላይ ተመሥርተን በምንሠራባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መክረናል ሲሉም ነው የጠቀሱት፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመልዕክታቸው ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሁዋዌም ለዚህ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እና ያለንን የሥራ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review