አዲስ አበባ የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት አሸነፈች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing አዲስ አበባ የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት አሸነፈች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!

አዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት UN-Habitat በቻይና ያዘጋጀውን የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት አሸነፈች!!

ይህ ድል ለአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው!

በተባበሩት መንግሥታት የሰዎች ሰፈራ ፕሮግራም (UN-Habitat) እና በቻይና ያተዘጋጀውን የሸንሃይ ሽልማት፣ በዘላቂ፣ አካታች፣ ሰው ተኮርና አይበገሬ የከተማ ልማት ውጤታማ ሥራዎችን ላከናወኑ በየዓመቱ ለአምስት ከተሞች የሚሰጥ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ነው። በዚህም አዲስ አበባ በ2026 ከተሸላሚ ከተሞች አንዷ ሆናለች።

ይህ ለከተማችን የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አይደለም። በ2024 በUN-Habitat እና በደቡብ ኮሪያዋ ሴኡል ከተማ የተዘጋጀው “የሴኡል ከተማ ሽልማት”አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።

እነዚህ ተከታታይ ዕውቅናዎች በከተማ ልማት የተከናወኑ ሥራዎችንና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያመለክታሉ።

የሸንሃይ ሽልማቱ በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑት የከተማ ልማት ሥራዎች ውጤታማነት፣ ዘላቂነትና ለነዋሪዎች ያላቸው ጠቀሜታ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን ያሳያል።

ለዚህ ስኬት ካበቋት ዋና ዋና የልማት አቅጣጫዎች መካከል፦

• ሰው ተኮር አቀራረብን ከከተማ መልሶ ማልማት ጋር በማቀናጀት የነዋሪዎችን ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት፤

• የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሻሻል የተከናወኑ ሥራዎች፤

• በከተማ ኮሪደሮችና በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች አካታችና የተቀናጀ ልማትን ማረጋገጥ፤

• የትራንስፖርት አገልግሎትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎች፤

• አረንጓዴነትን፣ ጽዳትንና የከተማ ውበትን በማሻሻል ምቹና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢ መፍጠር ይገኙበታል።

እነዚህ ተግባራት የከተማዋን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማሳደግና አዲስ አበባን ተወዳዳሪ ከተማ በማድረግ ረገድ ያላቸውን አስተዋጽኦ ያሳያሉ።

በተለይም በታዳጊ አገራት ከባድ ፈተና የሆነውን የከተማ መልሶ ማልማት በስኬት ማከናወን እንደሚቻል ያሳየችው ተሞክሮ፣ ለሌሎች ከተሞችም ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ ምሳሌ ሆኗል።

ይህ ድል የተግባር ስኬት፣ የጋራ ጥረትና የጋራ ውጤት ነውና ሁላችንም በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review