የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች ሚዛንን ጠብቆ መስራት ይጠበቅባቸዋል- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

You are currently viewing የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች ሚዛንን ጠብቆ መስራት ይጠበቅባቸዋል- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

AMN- ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም

የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች የሚዲያ ነጻነት እና ኃላፊነት መካከል ሚዛንን ጠብቆ መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያስገነባው የኢትዮጵያ ሚዲያ የልህቀት ማዕከል የምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች የሚዲያ ነጻነት እና ኃላፊነት መካከል ሚዛንን ጠብቆ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ነጻነት እና ተጠያቂነት የማይነጣጠሉ መሆኑን በመገንዘብ ሃሳብን የመግለጽ መብት እና ተጠያቂነትን ማዕከል በማድረግ ሚዲያዎች እና ባለሙያዎች መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

ሀገረ መንግስት እንዲጸና በሃላፊነት መስራትና ሙያዊ ታማኝነት አስፈላጊ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ምድር አይነኬነት የማይሰራ በመሆኑ የሚዲያ ተቋማት የሀገር እና የህዝብ ብሄራዊ ጥቅምን አክብረው መስራት አለባቸው ሲሉም አንስተዋል።

የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች ብሄራዊ ጥቅምን ማዕከል አድርጎ መስራት እንዲችሉ የተመረቀው የኢትዮጵያ ሚዲያ የልህቀት ማዕከል ለምክክር እና ለስልጠና ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review