በጫኝና አውራጅ ማህበራት እና በተርሚናል አገልግሎት የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮች እየተፈቱ ነው

You are currently viewing በጫኝና አውራጅ ማህበራት እና በተርሚናል አገልግሎት የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮች እየተፈቱ ነው

AMN- ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም

በጫኝና አውራጅ ማህበራት እና በተርሚናል አገልግሎት የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮች ሕግ እና መመሪያን መሰረት በማድረግ እየተፈቱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ፡፡

ቢሮው ከሰላም እና ፀጥታ አጋዥ ኃይሎች ጋር በ2019 በጀት ዓመት በአንደኛ ሩብ አመት የክትትል፣ የድጋፍና የሱፐርቪዥን ሥራዎች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል፡፡

በጫኝና አውራጅ ማህበራት እና በተርሚናል አገልግሎት የቅሬታ ምንጭ የነበሩ ችግሮች ሕግ እና መመሪያን መሰረት በማድረግ እየተፈቱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ገልጸዋል፡፡

በተርሚናል እና በፓርኪንግ አገልግሎት መስጫ ስፋራዎች ከዚህ በፊት የነበሩ የንጥቂያ እና የዘርፋ ተግባራትን መቀነስ እንደተቻለም ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በጫኝና አውራጅ ፣ በተርሚናል እና በፓርኪንግ አገልግሎት ላይ ማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ የግንዛቤ ማሳደጊያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጉማታው ገዳሙ በበኩላቸው፤ የሰላም እና ፀጥታ አጋዥ ኃይሎች ከሕብረተሰቡ ጋር በመሆን የአጋዥነት ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከጫኝና አውራጅ፣ ከተርሚናል እና ከፓርኪንግ አገልግሎት ማህበራት የተወጣጡ የውይይቱ ተሳታፊዎችም፤ የተሰጠንን የሥራ ዕድል በመጠቀም በአካባቢያችን ምንም አይነት የስርቆ፣ የንጥቂያ እና ሌሎች መሰል ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ቀድሞ የመከላለክ ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

#ትልቅሃገር#ትልቅህዝብ#ታላቅርዕይ#አዲስሚዲያኔትዎርክ#የትዉልድድምጽ#አዲስአበባ#ኢትዮጵያ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review