ኮፕ 31 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምትሰራውን ስራ ለዓለም ለማሳወቅ ያግዛል- ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኮፕ 31 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምትሰራውን ስራ ለዓለም ለማሳወቅ ያግዛል- ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

AMN- ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም

የተባበሩት መንግሥታት አየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 31) “ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባርና አፈጻጸም መሸጋገር” በሚል መሪ ሀሳብ በቱርክዬ አንታሊያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ቱርክዬ ይገኛል።

ጉባኤውን ተከትሎ መልዕክት ያስተላለፉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፤ ኮፕ 31 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አጠቃላይ የምታከናውነውን ተግባር ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ቀጣዩን ኮፕ 32 የምታስተናግድ ሀገር በመሆኗ በጉባኤው ማሳካት የምትፈልጋቸውን ቁልፍ ግቦች አብራርተዋል።

በኮፕ 31 የሚኖረው ሂደት ውጤታማ ሆኖ ቀጣዩን ኮፕ 32 ይበልጥ ስኬታማ ሊያደርግ የሚችል ጠንካራ መደላደል መፍጠር ዋነኛው ዓላማ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ከቱርክዬ እና ከአውስትራሊያ ፕሬዚዳንቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ለኮፕ 32 ስኬት አጋር ከሚሆኑ አካላት ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር እና ስለ ሀገሪቱ ዓላማና ሀሳብ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን ኮፕ 32 በጉጉት እንዲጠብቅና በጉባኤው ላይ ሰፊ ቁጥር ያለው ታዳሚ እንዲገኝ ማድረግ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በትዝታ መንግስቱ

#EthiopiaAtCOP31#COP31#GreenDevelopment#ClimateActionAfrica#COP32#addismedianetwork#Ethiopia#addisababa

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review