በኢትዮጵያና ኖርዌይ መካከል በአየር ንብረት ለውጥና COP32 ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

You are currently viewing በኢትዮጵያና ኖርዌይ መካከል በአየር ንብረት ለውጥና COP32 ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

AMN- ኅዳር 1/2019 ዓ.ም

ትላንት ከተጀመረው COP31 ጎን ለጎን፣ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሚኒስትርና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ ከኖርዌይ የአየር ንብረትና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሲግሩን ጄርሎው አስላንድ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የብሉምበርግ ፕላንትሮፒ ኢኒሸቲቭ ፎር ግሎባል ሮድሴፍቲ ጎን ለጎን ነው።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ሚኒስትሮች በተለይም ለCOP32 ዝግጅት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ፍላጎት የገለፁ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር ሥር የሚከናወኑ የደን ልማት ጥረቶችን ማስፋፋት እና ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ያላቸውን አስተዋጽኦ ማጉላት ያለውን አስፈላጊነት ተነጋግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review