በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን አመራሩ በአገልግሎት አስጣጥ መድገም ይገባዋል፡-ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) አሳሰቡ ::

You are currently viewing በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን አመራሩ በአገልግሎት አስጣጥ መድገም ይገባዋል፡-ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) አሳሰቡ ::

AMN – ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም

በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን አመራሩ በአገልግሎት አስጣጥ መድገም እንደሚገባዉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር(ዶ/ር) አሳሰቡ ፡፡

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በየደረጃዉ ለሚገኙ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ::

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ባለፉት ዓመታት ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር እና አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸዉን ተናግረዋል ::

ህዝቡ ከሚፈልገዉ አገልግሎት አንፃር ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ የተናገሩት ሃላፊዉ ህብረተሰቡን በተቀመጠዉ መስፈርት መሰረት ማገልገል ይገባል ብለዋል ::

በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን በአገልግሎት አስጣጥ መድገም እንደሚገባም አሳስበዋል ::

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል አመራሩ የተጣለበትን ኃላፊነት ተረድቶ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ይገባልዋ ብለዋል ::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review