ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡-ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

You are currently viewing ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡-ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም

ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮን እና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ለኤኤምኤን በላከው መግለጫ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኝውም አይነት ድሮን ያለ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን የተላለፈውን ማሳሰቢያ በማያከብሩ አካላት ላይ እርምጃ

እየተወሰደ ይገኛል ብሏል፡፡

በተለይ ከአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቅንጅታዊ ስምሪቱን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኝውም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፤ ብዙዎችም ይህን ተግባራዊ

እያደረጉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ማሳሰቢያውን በመጣስ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮን ለማስነሳትና ለማብረር ሙከራ ያደረጉ አካላትን በጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመለየት ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ከማድረግ ጀምሮ ተገቢው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ያመለከተው መግለጫው፤ በተለይ የአፍሪካ

ሕብረት ጉባዔ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን ስጋቶች ለመከላከል የሚያስችል በቂ የቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱን አስታውቋል፡፡

ከሥራ ጋር በተያያዘ ድሮኖችን መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በ+251 983 00 02 98 እና +251 983 00 04 01 ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚችል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን የላከው መግለጫ ያሳሰበ ሲሆን፤ ያለፍቃድ በሚኒሱ እና በሚበሩ ድሮኖች ላይ የሚደረገው ቁጥጥርና

የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review