AMN-የካቲት 15/2017 ዓ.ም
ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሥራ ኃላፊዎቹ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የለውጥ ሥራዎች እንዲሁም የባሕርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየተሠሩ ያሉ የለውጥ ሥራዎች ተስፋ ሰጪና የሚበረታቱ መሆኑ መገለጹንም የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡