የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ

You are currently viewing የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ

AMN – መጋቢት 17/2017

የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታዎች ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) እና ቸሩጌታ ገነነ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

በዚሁ መድረክ የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመስርቷል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፎረሙ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለጋራ ሰላም እና አንድነት የሚሰሩበት ነው።

እንዲሁም በጋራ እሴቶቻቸው እና የወንድማማችነት ግንኙነትን ለማጠናከር የሚመክሩበት መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review