በርካታ አርሶ አደሮች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተሸጋግረዋል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing በርካታ አርሶ አደሮች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተሸጋግረዋል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ዱርሲቱ ቢሊሱማ ቀበሌ የበጋ ስንዴ ልማት ማምረት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተሸጋግረዋል፡፡

በወረዳው በ17 ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የበጋ ስንዴ ልማት ስራዎችን በ5000 ሄክታር መሬት ላይ እየሰሩ ይገኛል፡፡ ቀደም ሲል የዝናብ ወቅት ተጠብቆ ይሰራ ከነበረው የስንዴ ግብርና ስራ አርሶአደሮች ተላቀው በአሁን ሰዓት በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል፡፡

በወረዳው በ14 ክላስተር 5400 አባወራዎች በስንዴ ልማት ምርት ተደራጅተው እየሰሩ እንደሚገኙ እና በአንድ ሄክታር ከ70 እስከ 80 ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚያገኙ ተጠቅሷል፡፡

አርሶ አደሮቹ ቀደም ሲል በሴፍትኔት በነፍስ ወከፍ በወር እስከ 15 ኪሎ ግራም ስንዴ ይሠፈርላቸው እንደነበርና አሁን ላይ ግን በራስ አቅም ማምረት እና መጠቀም በመቻላቸው ከተረጂነት ስሜት ተላቀው ቤተሰቦቻቸውን በአግባቡ መምራት ችለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የበጋ ስንዴ እርሻ በአካባቢያው የማይታወቅ ሲሆን ዛሬ ግን መንግስት ባስጀመረው ኢኒሼቲቭ እና ባደረገው ድጋፍ አርሶ አደሮች የተሻለ የምርት አቅርቦት እንዲኖራቸው በማድረግ ምርታማነቱ በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

በዚህም ቀደም ሲል በደህነት ሳቢያ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ የማይልኩ የነበሩ አርሶ አደሮች ዛሬ ላይ በ107 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ12 ሺህ በላይ ልጆች ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲከታተሉ ማድረግ ችለዋል፡፡ – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review