ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ካሉት የእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ሰአር ጋር በኢትዮ-እሥራኤል ግንኙነት ላይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
“ሁለቱ ሀገሮቻችን በታሪክ ሥረ መሠረት ላይ የተገነባ ረዥም ዘመን የቆየ ግንኙነታቸውን ዛሬም ቀጥለዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዛሬ ትብብራችን በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በዲፕሎማሲያዊ፣ በማኅበራዊ እና በሌሎችም መስኮች ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል” ሲሉም ገልጸዋል።