የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም ክፍት ተደረገ

You are currently viewing የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም ክፍት ተደረገ

AMN ሚያዝያ 9/2018

የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ኢራን አስታወቀች

በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ባለበት ጊዜ ሁሉ ማንኛውም የንግድ መርከብ ያለምንም እንቅፋት በወሽመጡ ማለፍ እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ኢራን ጊዜያዊ የተኩስ አቁምን እንደማትቀበልና ይልቁንም በመላው ቀጣናው ለተቀሰቀሰው ጦርነት ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review