13ኛው ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

You are currently viewing 13ኛው ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

AMN-ግንቦት 18/2017 ዓ.ም

ዛሬ በተጀመረዉ ሻምፒዮና የተለያዩ የፍፃሜና የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል::

በሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል በተደረገ የፍፃሜ ውድድር አለምናት ዋለ ከአማራ ፖሊስ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡

ኬና ቱፋ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 2ኛ ፤ ዘሪቱ ዳባ ከሸገር ሲቲ 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል::

በወንዶች በተደረገ 3000 ሜትር መሰናክል ዲንቃ ፍቃዱ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ቀዳሚ ሆኖ መግባት ችሏል::

ሀይሉ አያሌው ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 2ኛ ፤ ጀማል ጁሀር ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 3ኛ ደረጃ ይዘው ጨርሰዋል፡፡

የጦር ውርወራ በሁለቱም ፆታ ፤ በወንዶች ከፍታ ዝላይ የፍፃሜ ውድድሮች ተደርገዋል፡፡

የውድድሩ የከሰዓት መርሃግብር ከ10 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review