መርማሪው ብዕር

You are currently viewing መርማሪው ብዕር

AMN- ግንቦት 29/2017 ዓ.ም

በዓለም እስከ አሁን 10 ሚሊየን ሰዎችን እንዳጠቃ የሚገለጸውን የፓርኪንሰን ህመም መርምሮ ለመለየት ያስችላል የተባለለትን ብዕር የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች ማግኘታቸው ተሰምቷል።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) የተገጠመለት ብዕሩ፣ የእጅ ፅሁፍ በማበላሸት የሚታወቀውን የፓርኪንሰን ህመም በቀላሉ ይለያል ነው የተባለው።

በህመሙ በተጠቁ ሰዎችና ነፃ በሆኑት መካከል በተደረገው የሙከራ ምርመራ 95 በመቶ የተሰካ ውጤት መመዝገቡም ተመላክቷል።

እንደ ዘ ኢንድፔንደንት ዘገባ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት በዘርፉ ስፔሻላይዝ ያደረገ ሀኪም ባለመኖሩ ምክንያት በነዚህ ሀገራት ያሉ የፓርኪንሰን ህመምተኞችን ለማወቅ አዳጋች ነው።

ይህ መርማሪ ብዕር ግን በአነስተኛ ዋጋ የሚገኝ በመሆኑ ችግሩን እንደሚቀርፍ ተስፋ ተጥሎበታል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review