ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለትን፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እና የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን መረቁ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለትን፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እና የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን መረቁ

AMN ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል።

እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል።

‎ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰድ የጠቅለይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review