አርሰናል በኤብሪቼ ኤዜ ግብ ወደ መሪነቱ ተመለሰ

You are currently viewing አርሰናል በኤብሪቼ ኤዜ ግብ ወደ መሪነቱ ተመለሰ

AMN- ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም

አርሰናል በ34ኛ ሳምንት የሊግ መርሃግብሩ በሜዳው ኤምሬትስ ኒውካስትል ዩናይትድን አስተናግዶ 1ለ0 አሸንፏል።

ኤብሪቼ ኤዜ የመድፈኞቹን ድል እውን ያደረገች ብቸኛ ግብ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል። እንግሊዛዊው የአጥቂ አማካይ የውድድር ዓመቱ 10ኛ ግቡ ሆኖ ተመዝግቧል።

አርሰናል ድሉን ተከትሎ በማንችስተር ሲቲ ተወስዶበት የነበረውን መሪነት መልሶ አግኝቷል። የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ34 ጨዋታዎች 73 ነጥብ ሰብስቦ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል። አንድ ቀሪ ጨዋታ ካለው ማንችስተር ሲቲ በሦስት ነጥብ ርቋል።

አርሰናል በቀጣይ ሳምንት አጋማሽ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

በጨዋታው በአርሰናል በኩል ካይ ሃቨርትዝ ጉዳት ገጥሞት ተቀይሮ ወጥቷል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በቁልቁለት ጉዞው ቀጥሏል። የዛሬ ሽንፈት በሊጉ የደረሰባቸው 16ኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review