በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የተመራ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ቡድን በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስራ ምልከታ እያደረገ ነው።
የኤ ኤም ኤን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ የሚዲያው የስራ ኃላፊዎች የተቋሙን የለውጥ ጉዞ ለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ቡድኑ አብራርተዋል።
ኤ ኤም ኤን በመዲናዋ የተከናወኑ አበይት ክስተቶችን ከጠያቂ መሰናዶዎችና ዘጋቢ ፊልሞች ጋር አዋህዶ ሚዛኑን በጠበቀ የጋዜጠኝነት ሙያ በተለያዩ ቋንቋዎች በመላው ዓለም ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የስራ ምልከታው መንግስት ሚዲያውን ለመደገፍና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል የሚያከናውናቸው የለውጥ ስራዎች አካል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናግረዋል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአዲስ ቲቪ፣ የኤፍኤም 96.3 ራዲዮ እና የአዲስ ልሳን ጋዜጣ እንዲሁም የሁሉም ዲጂታል ሚዲያዎች ባለቤት ነው።
በካሳሁን አንዱዓለም