የፀጥታ አካላት በእውቀታቸው እና በመስዋዕትነታቸው የኢትዮጵያን ሰላም እንዲያፀኑ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing የፀጥታ አካላት በእውቀታቸው እና በመስዋዕትነታቸው የኢትዮጵያን ሰላም እንዲያፀኑ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ሰኔ 14/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላትና የፖሊስ ሠራዊቶች በእውቀታችሁ፣ በላባችሁና በመስዋዕትነታችሁ የኢትዮጵያን ሰላም እንድታፀኑ ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ::

ፕሬዝዳንት ታየ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከመላው ሀገሪቱና ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የተወጣጡና በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስለጠናቸው የፖሊስ አባላት ባስመረቀት ወቅት መልዕክቱን ያስተላለፉት።

ኢትዮጵያ ወደ ዕድገት በምታዳርገው ግስጋሴ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ አሁንም እንቅፋት ለመሆን ጥረት ቢያደርጉም የፀጥታ አካሉ ከህዝቡ ተባብሮና ተቀናጅቶ በመስራቱ የሀገርን ሠላም ማስጠበቅ ተችሏል ያሉት ፕሬዝዳንት ታየ አሁንም የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላትና የፖሊስ ሠራዊቶች በእውቀታችሁ፣ በላባችሁና በመስዋዕትነታችሁ የኢትዮጵያን ሰላም እንድታፀኑ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው አጠቃላይ 1 ሺህ 348 ሰልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 7 ያህሉ የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የፖሊስ አባላት ተመራቂዎች ናቸው ተብሏል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review