አሁን ያለው ሥርዓት ኢራንን ታላቅ ሀገር ማድረግ ካልቻለ የአገዛዝ ለውጥ እንዴት ሊኖር አይችልም ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋል፡፡
አሜሪካ በቀጥታ መሳተፍ በጀመረችበት የኢራን-እስራኤል ግጭት የጦር አውሮፕላኖቿን በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎችን በመላክ ጥቃት ማድረሷ ይታወቃል፡፡
አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር መሠረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ የማጥፋት አቅም አላቸው የተባለላቸውን ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን በብቸኝነት እንዳላት ይገለፃል፡፡
ከሰሞኑ በኢራን በሚገኙ ሶስት ወሳኝ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት ውድመት ማስከተሏን ፕሬዝዳንት ትራምፕ የገለፁ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን የጥፋቱ መጠን አለመታወቁን አስታውቋል፡፡
እስራኤል ግጭቱ እራስን የመከላከል እንጂ በኢራን የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት አይደለም ስትል በተደጋጋሚ ጊዜ ገልፃለች፡፡ የጦርነቱ ግብ የሥርዓት ለውጥ ማምጣት አይደለም፣ ነገር ግን ውጤቱ እንደዚያ ሊሆን ይችላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ መናገራቸውም ለዚሁ ይመስላል፡፡
እስራል ጦርነቱ እራስን የመከላከል ነው ትበል እንጂ አጋሯ አሜሪካ በኢራን የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል በፕሬዝዳንቷ በኩል ጠቆም አድርጋለች፡፡
አሁን በኢራን ያለው ሥርዓት ኢራንን ታላቅ ማድረግ ከተሳነው እንዴት የሥርዓት ለውጥ ላይኖር ይችላል ሲሉ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተናገሩት፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራን አምባሳደር አሜሪካ በማይረባ ምክንያት ለጦርነቱ ድጋፍ መስጠቷን መክሰሳቸውን ቢቢሲ ነው የዘገበው፡፡
ሆርሙዝ የተሰኘውን ሰርጥ ኢራን እንዳትዘጋው ቻይና ግፊት እንድታደርግባት አሜሪካ መጠየቋም የሚታወስ ነው፡፡