የኢትዮጵያ ብልፅግና ከዳር እስከ ዳር እስኪዳረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ብልፅግና ከዳር እስከ ዳር እስኪዳረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN – ሐምሌ 6/2 የ2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በዛሬው የአሶሳ ጉበኝታችን አዲሰ አበባ ላይ ከዓመት ዓመት ባህል እየሆነ የመጣውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የምገባ ማዕከል ማቋቋም፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አካል የሆነው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታን እና የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራዎችን አሶሳ ከተማ ላይ አስጀምረናል ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትራችን የስራ አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባን አሮጌ ገጽታ እና የድህነት ታሪክ ለመቀየር በመልሶ ማልማት እና በኮሪደር ልማት ስራ ከህዝብ ውይይት እስከ ትግበራ 24/7 በመስራት እንዲሁም ህዝባችንን የልማቱ ባለቤት በማድረግ ያመጣነውን ተጨባጭ ወጤት እና ተሞክሮዎቻችንን አካፍለናል ሲሉም አክለዋል።

ወደ ክልሎች እየተስፋፋ ያለውን እና በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለዉን የኮሪደር ልማት የክልሉ ፕሬዝዳንት አሻድሊ ሃሰን አስጎብኝተውናል ሲሉም ነው የገለጹት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review