የኢትዮጵያ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ተመሰረተ

You are currently viewing የኢትዮጵያ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ተመሰረተ

AMN – ሐምሌ 13/ 2017 ዓ.ም

‎ፎረሙ የተመሰረተው በኢትዮጵያ ውስጥ በምርምር ስራ ላይ በመሳተፍ ላይ በሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ነው።

‎የፎረሙ ሰብሳቢ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር)፣ የትብብር ፎረሙ አቅምና እውቀትን በማሰባሰብ ችግር ፈቺ እንዲሁም የሳይንስ እና ፈጠራ ውጤቶችን ለፖሊሲ አውጪዎች ለማቅረብ ያግዛል ብለዋል።

‎በተመሠረተው ፎረም መሠረት በጋራ ሀብት ማሰባሰብ፣ የምርምር መሠረተ ልማቶችን በጋራ መጠቀም፣ የእውቀት ሽግግር እና ተሞክሮዎችን መለዋወጥም ይገኝበታል ተብሏል።

‎ፎረሙ ውጤታማ እንዲሆን ከአባላቱ እና ባለድርሻ አካላት ብዙ እንደሚጠበቅም ሰብሳቢው ዶከተር አስራት መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review