ሦስት አራተኛው ስራችን እየተጠናቀቀ ነው – ም/ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ

You are currently viewing ሦስት አራተኛው ስራችን እየተጠናቀቀ ነው – ም/ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ

AMN – ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በአብዛኛው ሦስት አራተኛው ሥራ መጠናቀቁን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ፣ ኮሚሽኑ ያቀደውን ስራ በሚገባ እና በጠበቀው ልክ እያከናወነ ይገኛል።

በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙት ስምንት የምክክር ቡድኖች ለቀናት በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው፣ በዛሬው ዕለት አብዛኞቹ በምክረ-ሀሳቦቹ ላይ ተስማምተው ፊርማቸውን በማስቀመጥ ስራቸውን እያጠናቀቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በቀጣይም እነዚህ ስምንት የምክክር ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች የሚያጣጥም፣ የሚቃረኑ ነገሮች እንዳይኖሩ የሚከታተሉ እንዲሁም ድግግሞሾችን በማስወገድ ምክረ-ሀሳቦቹ አንድ ወጥነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን ተናግረዋል።

ይህ ቡድን ስራውን በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ እንደሚጀምርም ነው የገለጹት።

በሌላ በኩል፣ ከግለሰቦች፣ ከቡድኖች እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በተመለከተ ኮሚሽኑ በተዘረጋው የቅሬታ መፍቻ ስነ-ስርዓት መሰረት እየተቀበለና እያጠና ውሳኔ እየሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review