የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ ይገኛል

You are currently viewing የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ ይገኛል

AMN – ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ እንሚገኝ የቢሮው ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ረታ ገልጸዋል።

የቢሮው አመራሮች ፣ ሠራተኞች ፣ የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮችና በጎ ፈቃደኛ ሕብረተሰብ ክፍሎች በጋራ በመሆን የደም ልገሳ አድርገዋል።

አቶ ብርሀኑ ረታ ቢሮው ከዋና የስራ ኃላፊነቱ ባሻገር ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ የተለያዩ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማከናወን ማህበራዊ ተግባራትን በመደገፍና በመሳተፍ የአንድነት፣ የመረዳዳትና የሰብዓዊነት እሴቶችን ለማጠናከር እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የደም ልገሳው ህብረተሰቡ በችግር ጊዜ የሚያሳየውን መረዳዳትና የመተጋገዝ ባህል ለማጠናከር እንዲሁም በደም እጥረት ምክንያት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳያጡ መታደግን በማሰብ የተካሄደ መሆኑን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ደም መለገስ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሊያደርገው ከሚችለው ትልቅ የሰብዓዊነት ተግባር አንዱ መሆኑን የጠቀሱት የደም ልገሳው ተሳታፊዎች ፣ ሌሎችም ደም ልገሳ በማድረግ ደም የሚፈልጉ ወገኖችን ህይወት ማዳን እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review