የኢንስቲትዩቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተቋሙን ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግና በጋራ መስራት በጋራ መዘጋጀት አለብን ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው የሥልጠና ፣ የምክር እና የጥናትና ምርምር እና ሌሎችም አገልግሎቶች ዘመናዊ እና ለሀገር ጠቀሚታ ያላቸው እንዲሆኑ የተቋሙ ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱን እንደ አዲስ ለማዋቀር በአዋጅ ቁጥር 5313/2017 ለኢንስቲትዩቱ የተሰጠው ሀገራዊ ኃላፊነት በጋራ ለመወጣትም እያንዳንዱ ባለሙያ ድርሻውን መውጣት እንዳለበት አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በደብረዘይት / ቢሾፍቱ / የስልጠና ማዕከል ውይይት አካሄዷል።
በውይይቱ የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞችም ተቋሙን በአፍሪካ እውቅና ያለው የላቀ የሥራ አመራር ልማትና የመማር ማዕከል ለማድረግ የያዘውን ራዕይ ለማሳካት ዘመኑ የሚፈልገውንና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
በዳንኤል መላኩ