ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን የ14 ዓመት ጉዞ፤ በተለይም የህዝቡን ተሳትፎ የሚያሳይ የፎቶ፣ የስዕል እና በአባይ ዙሪያ የተፃፉ መፃህፍት አውደ ርዕይ እና ፓናል ውይይት አካሂደናል ሲሉ ገልፀዋል።

በፖናል ውይይቱ የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለዉ ፋይዳ፣ ከጂኦስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና መሸጋገር፣ የህዝብ አንድነትና ተሳትፎ ትርጉም አስመልክቶ በምሁራን ትንታኔ መቅረቡን ከንቲባዋ ገልፀዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 14 ዓመታት ያለፈበት ውጣ ውረድ፣ የተገኙ ድሎች፣ የውሃ ፖለቲካ ምንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ወይይት ተካሂዷል።