የህዳሴ ግድቡ ትናንት የነበረውን የኢትዮጵያ የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ”ኢትዮጵያ ችላለች” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የህዳሴ ግድብ ሃሳባዊ ሃይሉ ብርቱ፤ መልእክቱም እንችላለን ነው በማለት የተሰጡንን መዘባበቻ ቅጥያ ስም አሽቀንጥረን ለመጣል ከወሰንን እንችላለን ብለዋል፡፡
የህዳሴ ግድቡ ትናንት የነበረውን የኢትዮጵያ የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡
በሊያት ካሳሁን