‎ኢሬቻ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ከማቀራረብና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ከመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጾኦ እንዳለዉ ተገለጸ

You are currently viewing ‎ኢሬቻ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ከማቀራረብና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ከመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጾኦ እንዳለዉ ተገለጸ

AMN-መስከረም 20/2018 ዓ.ም

ከሃገር ዉስጥና ከዉጭ ሃገር በርካታ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ከማቀራረብና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ከመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጾኦ እንዳለዉ ተገለጸ፡፡

‎የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የሚያሰናዳው 45ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን የኢሬቻን ባህላዊ እሴቶች የተመለከተ የመወያያ ጽሁፍ በምሁራን ቀርቦ ሙያዊ ተካሂዶበታል፡፡

‎የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ቀን መሆኑን አንስተዋል፡፡ የዘንድሮዉ የሆረ ፊንፊኔና የሆረ ሃርሰዲ የኢሬቻ በአል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ እንደሚከበርም አንስተዋል፡፡

‎በኢሬቻ እሴቶች ላይ ያተኮረዉን የውይይት ጽሁፍ ያቀረቡት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ መሃመድ ነሞ (ዶ/ር) ኢሬቻ የኦሮሞ የምስጋና በአል ስለመሆኑ አብራርተው ‎ኢሬቻ ባለፈው ዘመን ስለተደረገው ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት፣ ስለሚመጣው ጊዜም ያማረ ነገር እንዲሆን ጸሎት የሚያቀርቡበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ኢሬቻ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን በማቀራረብ ፤ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በመስበክ ሀገሪቱን ለተቀረው ዓለም የሚያስተዋዉቅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነው ብለዋል።

‎ኢሬቻ ድንበር የለውም ያሉት ተመራማሪው የኦሮሞ ህዝብ ዕድሜ፣ ጾታ፣እምነት፣ አካባቢ ሳይገድበው በአንድ ነት ተሰባስቦ ባህሉን የሚያንጸባርቅበት፤ ወንድማማችነቱን የሚያጠናክርበት ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‎በ-ምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review