ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበረንን ቆይታ አጠናቀን ወደ አዲስ አበባ ተመለሰን የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብለናል ብለዋል፡፡
ሁለቱ ሀገሮቻችን የዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት አለን። በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙንን ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡