በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት እና በሰንደቅ ዓላው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ምን ያሳያል?
1. አረንጓዴው ቀለም፡- የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡
2. ቢጫው ቀለም፡- የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው፡፡
3. ቀዩ ቀለም ፡- ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡
እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ
1. ክብ የሆነው፡- ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡
2. ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች፡- የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ፡፡
3. ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፡- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያመላክታል፡፡
4. ቢጫ ጨረሩ ደግሞ ፡- በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል፡፡
18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡
ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው።