በ2018 በጀት ዓመት፣ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቱሪዝም ዘርፉ ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ ተደርጓል

You are currently viewing በ2018 በጀት ዓመት፣ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቱሪዝም ዘርፉ ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ ተደርጓል
  • Post category:ቱርዝም

AMN ህዳር 25/2018

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቱሪዝም ዘርፉ ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ መደረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ ጉባዔዎች በአጠቃላይ ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ መደረጉን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ በጀት ዓመት በተካሄዱት የሀገር ውስጥ የአደባባይ በዓላት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ከ376 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች መዲናዋን መጎብኘታውንም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ለተገኘው ገቢ ትልቅ አስተዋጽዖ አላቸው ያሉት ኮሚሽነር ሁንዴ የልማት ስራው የከተማዋን ብሎም የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ የቀየረ ነው ብለዋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፉ የከተማዋን ኢኮኖሚ ከማነቃቃት አንጻር ሚናው ላቅ ያለ ስለመሆኑ ያነሱት ኮሚሽነሩ ከኢኮኖሚው ባሻገርም በዲፕሎማሲው የከተማዋን መልካም ገጽታ ከመገንባት አንጻር ያለው ሚና ከፍተኛ ነው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እና ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review